Posted: Sep 14, 2025

Full time

Career Level: Senior(5-8 years)
Salary:
Location: Addis Ababa
Deadline: Sep 25, 2025
Expired

የሥራ መደቡ መጠሪያ፡- የሽያጭ ዋና ክፍል ኃላፊ (Sales Division Head) 

የሥራ ክፍል፡- የሽያጭ እና ማርኬቲንግ መምሪያ

ቀጥታ ተጠሪነት፡- ለሽያጭ እና ማርኬቲንግ ሥራ አስኪያጅ 

የስራ ቦታ፡ መርካቶ የሽያጭ ቢሮ
ብዛት - 02

የሥራ መደቡ ዋና ዋና ተግባራትና ኃላፊነት

የድርጅቱን አጠቃላይ የሽያጭ ስትራቴጅዎችንና ስልቶችን እንዲሁም ሽያጭን ለመጨመር የዕድገት እቅዶችን ያዘጋጃል፤ይመራል፤ይተገብራል፡፡ የሽያጭ ቡድንንና ማዕከላትን በማስተባበርና በመምራት እንዲሁም የታዩ ክፍተቶችን በመለየት የሽያጭ ሰራተኞችን ከማርኬቲንግ ክፍልና ከመምሪያዉ ጋር በመሆን በማሰልጠን የድርጅቱን የሽያጭ ግብ ለማሳካት ይሰራል፡፡

ዝርዝር ተግባራትና ኃላፊነት

  • ከድርጅቱ የቢዝነስ ዓላማ ጋር የሚሄድ የሽያጭ ስትራቴጂ በማዘጋጀትና በማጸደቅ ይተገብራል፡፡
  • የገበያ አዝማሚያዎችን፣ የተፎካካሪ ድርጅቶች የስራ እንቅስቃሴ እና የደንበኞች ፍላጎትን በመረዳት የድርጅቱን እድገትየሚያመጡ የሽያጭ ስትራቴጂዎችን ይተገብራል፡፡
  • በስሩ ያሉ የሽያጭ ሰራተኞችን ይመራል፣ይቆጣጠራል እንዲሁም ግልፅ የሆነ የአፈፃጸም መመዘኛ በማዘጋጀትይመዝናል፣ያግዛል፡፡
  • የገበያ አቅም ባላቸዉ የአ/አ እና ክልል ከተሞች ላይ የሽያጭ ማዕከላትን መክፈትን ጨምሮ ወኪል አከፋፋዮችንከማርኬቲንግ ክፍልና መምሪያዉ ጋር በመሆን ይመለምላል፡፡
  •  ከቁልፍ ደንበኞች፣ወኪል አከፋፋዮችና ቢዝነስ አጋሮች ጋር ጠንካራ የስራ ትስስር በመፍጠር የድርጅቱን ሽያጭ ያሳድጋል፡፡
  • የድርጅቱን የቀን፣የወርና ዓመታዊ የሽያጭ ግቦችን ለማሳካት ይሰራል፡፡
  • የደንበኞች አያያዝን በተሟላ መልኩ ይቆጣጠራል፣ የዋና ዋና ደንበኞች ዳታቤዝም በየጊዜዉ ያዘጋጃል፡፡
  • የሽያጭ ሪፖረቶችን፣ የደንበኛ ዝርዝር መረጃ እና አጠቃላይ የሽያጭ እንቅስቃሴን ለመምሪያዉ ስራ አስኪያጅ በሚሰጠዉመርሃ ግብር መሰረት ያቀርባል፣ይወያያል፣ለሚገጥሙት ተግዳሮቶች የመፍትሔ ሃሳቦችን ያቀርባል፡፡
  • ከምርት አቅርቦት ጋር በቅርበት በመነጋገር ሁሉም ምርቶች በተገቢዉ ጊዜና ቦታ መገኘታቸዉን በመከታተል የደንበኞችንእርካታ እና ሽያጭን ያሳድጋል፡፡
  • ከሌሎች የድጋፍ ሰጪ ክፍሎች ጋር በትብብር ይሰራል፡፡
  • በመምሪያዉ የሚሰጡትን ሌሎች ስራዎችን ያከናዉናል፡፡

ተፈላጊ ችሎታና የትምህርት ዝግጅት

የትምህርት ደረጃ- በሴልስ ማናጅመንት፣ማርኬቲንግ ማናጅመንት፣ቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን ወይም ተያያዥ ቢዝነስ መስክ የመጀመሪያ ድግሪ

የስራ ልምድ- 5 ዓመት እና በላይ በሙያዉ የስራ ልምድ ያለዉ ሆኖ ከዚህ ዉስጥ ቢያንስ 2 ዓመትና ከዚያ በላይ በኃላፊነት የሰራ፡፡ በፎም እና መርቻንዳይዚንግ ዕቃዎች ላይ የስራ ልምድ ያለዉ/ያላት/ ቢሆን የበለጠ ተመራጭነት አለዉ፡፡

ልዩ ክህሎትና ሥልጠና- መሰረታዊ የኮምፑዩተር ስልጠና ያለዉ፣ የማሳመንና ዉጤት ተኮር ስራ የመስራት፣ሽያጭንና የሽያጭ አዝማሚያዎችን መተንተን፣ የሽያጭ ቡድንን የማስተባበርና የመምራትና የሽያጭ ግብን የማሳካት፤የደንበኞች ትስስር እና ጥሩ ተግባቦት ያለዉ/ያላት/ አብሮ መስራትና የሌሎችን ማበረታታት የሚችል/የምትችል/

How To Apply

How to Apply:

If you are passionate about contributing to a rapidly growing company and have the required skills and qualifications, we encourage you to submit your applications, including a detailed CV and cover letter to amagaplc2021@gmail.com  with in 10 calendar days of the announcement.

Or you can send your application to the following address:

Amaga building, 3rd floor, Office No 305

Addis Ketema Sub City, Woreda o6, H. No 752, Chew Brenda Burkina Faso Street

P.O.BOX: 25968

Tel: +251-11-2760487/+251-11-2736635

Addis Ababa, Ethiopia 


Company Logo
Amaga Private Limited Company
View Jobs by This Company
Discover More Jobs

Explore other opportunities and find your next job.

View Other Jobs

© 2025 GeezJobs. Made by Geez-Tech.