Marketing Division Head

Amaga Private Limited Company

Posted: Sep 14, 2025

Full time

Career Level: Mid Level(3-5 years)
Salary:
Location: Addis Ababa
Deadline: Sep 25, 2025
Expired

የሥራ መደቡ መጠሪያ፡- ማርኬቲንግ ዋና ክፍል ኃላፊ (Marketing Division Head)

የሥራ ክፍል፡- የሽያጭ እና ማርኬቲንግ መምሪያ
ቀጥታ ተጠሪነት፡- ለሽያጭ እና ማርኬቲንግ ሥራ አስኪያጅ
የስራ ቦታ፦ ዋናዉ መስሪያ ቤት

ብዛት- 02

የሥራ መደቡ ዋና ዋና ተግባራትና ኃላፊነት

የድርጅቱን አጠቃላይ የገበያ ጥናት፤ ማስፋፊያ እና ማስተዋወቅ ስትራቴጅዎችን ያዘጋጃል፤ይመራል፡፡ ድርጅቱንና ምርቶቹን በተለያዩ አማራጮች በማስተዋወቅ አዳዲስ ደንበኞችን ወደ ድርጅቱ እንዲመጡ በማድረግ የድርጅቱን የገበያ ድርሻ ለማሳደግ ይሰራል፡፡ ለአዳዲስ ምርቶች መመረትና ነባር ሞዴሌች መሻሻል መረጃ ላይ በመመርኮዝ ይሰራል፡፡ የድርጅቱን ሁሉም ምርቶች ስርጭትና የገበያ ሁኔታ ይቆጣጠራል፤ከመምሪያዉ በሚሰጠዉ አቅጣጫ መሰረት በትብብር ይሰራል፡፡

ዝርዝር ተግባራትና ኃላፊነት

  • የድርጅቱን የቢዝነስ ዓላማ ሊያሳኩ የሚችሉ የግብይት ስትራቴጂና ዕቅድ አዘጋጅቶ በማፀደቅ ይተገብራል፡፡
  •  በስሩ ያሉትን ባለሙያዎች ይመራል፤ያስተባብራል፤ያለባቸዉን ክፍተት በየጊዜዉ እየለያ በማሰልጠን ያበቃል፡፡
  • ከንግድ አላማዎች ጋር የሚጣጣሙ የማስተዋወቂያ ዝግጅቶችን፣የንግድ ትርኢቶችን እና ኤግዚቢሽኖችን በመሳተፍ ድርጅቱንናምርቶቹን ያስተዋዉቃል፤የተሰሩ ማስታወቂያዎችም ያመጡትን ዉጤት ከመምሪያ ስራ አስኪያጅ ጋር በመሆን ይገመግማል፡፡
  • መረሃ-ግብር በማዉጣት የተለያዩ ድርጅቶችን በአካል በመሄድ አዳዲስ ደንበኞችን ወደ ድርጅቱ እንዲመጡ ያደርጋል፤ጨረታ የሚያወጡተቋማትን አስቀድሞ ትስስር በማድረግ ግንኙነቶችን ያጠናክራል፤የደንበኞችን የእርካታ ደረጃ በየጊዜዉ በመለካት የማሻሻያግብዓቶችንና ስትራቴጅዎችን በማዘጋጀት ይተገብራል፡፡
  • ድርጅቱ የሚያመርታቸዉ ምርቶች በተገቢዉ የጥራት ደረጃ መቅረባቸዉን ይቆጣጠራል፤ የግብዓት ምርጫዎች ላይ በመሳተፍ ተገቢዉንየጥራት ደረጃና ጊዜዉን ያማከለ ምርጫ ስለመሆኑ ያረጋግጣል፡፡
  • የድርጅቱ ሁሉም ምርቶች በመሸጫ መደብሮችና አከፋፋዮች መኖራቸዉን፣በተገቢዉ የማሳያ ቦታ መቀመጣቸዉን ይቆጣጠራል፤አዳዲስ የሽያጭ ማዕከሎችን ጥሩ የገበያ እንቅስቃሴ ያለበቸዉን የገበያ ቦታዎች በመለየት ያሰፋል፤ ወኪል አከፋፋዮችን ብቃትንመሰረት አድርጎ በመመልመል አብረዉ እንዲሰሩ ያደርጋል፡፡
  • የድርጅቱን ምርት ለማስተዋወቅ እና የገበያ ድርሻ እድሎችን ለማሳደግ የገበያ ጥናቶችን (የዋጋ፣የገበያ አዝማሚያዎችን፣የተፎካካሪድርጅቶች አቅርቦቶችን እና ሌሎችም) ያደርጋል፤ በተገኙት ግኝቶች መሰረትም ስትራቴጅዎችን በማዘጋጀት ይተገብራል።
  • የድርጅቱን ምርቶች በድርጅቱ ዌብሳይት፣ ማህበራዊ ሚዲያዎችና ሌሎች ዲጂታል አማራጮች ያስተዋዉቃል፤ይቆጣጠራል፡፡
  • በመምሪያዉ የሚሰጡትን ሌሎች ስራዎችን ያከናዉናል፡፡

ተፈላጊ ችሎታና የትምህርት ዝግጅት


የትምህርት ደረጃ- በማርኬቲንግ ማናጅመንት፣ዲጂታል ማርኬቲንግ ወይም ተያያዥ ቢዝነስ መስክ የመጀመሪያ ድግሪ

የስራ ልምድ- 5 ዓመት እና በላይ በሙያዉ የስራ ልምድ ያለዉ ሆኖ ከዚህ ዉስጥ ቢያንስ 2 ዓመትና ከዚያ በላይ በኃላፊነት የሰራ፡፡ በፎም እና መርቻንዳይዚንግ ዕቃዎች ላይ የስራ ልምድ ያለዉ/ያላት/ ቢሆን የበለጠ ተመራጭነት አለዉ፡፡

ልዩ ክህሎትና ሥልጠና- ማህበራዊ ሚዲያዎችንና ዌብሳይት በአግባቡ መጠቀምና ማስተዳደር የሚችል/የምትችል/፣ የገበያ ጥናቶችን በሚገባ መተንተንና ስትራቴጂ ማዘጋጀት የሚችል/የምትችል/፤የደንበኞች ትስስር እና ጥሩ ተግባቦት ያለዉ/ያላት/

How To Apply

If you are passionate about contributing to a rapidly growing company and have the required skills and qualifications, we encourage you to submit your applications, including a detailed CV and cover letter to amagaplc2021@gmail.com  with in 10 calendar days of the announcement.

Or you can send your application to the following address:

Amaga building, 3rd floor, Office No 305

Addis Ketema Sub City, Woreda o6, H. No 752, Chew Brenda Burkina Faso Street

P.O.BOX: 25968

Tel: +251-11-2760487/+251-11-2736635

Addis Ababa, Ethiopia


Company Logo
Amaga Private Limited Company
View Jobs by This Company
Discover More Jobs

Explore other opportunities and find your next job.

View Other Jobs

© 2025 GeezJobs. Made by Geez-Tech.