Posted: Nov 13, 2025
ContractJob Opportunity: የደህንነት ካሜራ ተቆጣጣሪ ባለሙያ position available at National Election Board of Ethiopia(NEBE) in አዲስ አበባ, Addis Ababa. Security, IT, Computer Science and Software Engineering jobs in Ethiopia are in high demand. Apply now through GeezJobs - Ethiopia's leading job portal.
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የደህንነት ካሜራ ተቆጣጣሪ ባለሙያ የስራ መደብ ላይ መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልቾችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።
የስራ መደብ መጠሪያ: የደህንነት ካሜራ ተቆጣጣሪ ባለሙያ
ብዛት: አንድ
ተጠሪነት: ለጠቅላላ አገልግሎት የስራ ክፍል ኃላፊ
የስራ ቦታ: አዲስ አበባ
የቅጥር ሁኔታ: በኮንትራት
ደመወዝ: በድርጅቱ ስኬል
አጠቃላይ የስራ ኃላፊነት
የደህንነት ካሜራ ተቆጣጣሪ ባለሙያው የቦርድ ቅጥር ግቢ ውስጥ የሰራተኞችን፣ የጎብኝዎችን እና የንብረትን ደህንነት ለመጠበቅ በደህንነት ካሜራ (ሲሲቲቪ ሲስተም) ቀጣይነት ያለው ክትትል እንዲደረግ እና ማንኛውንም አጠራጣሪ ወይም ያልተለመደ ተግባር በፍጥነት ሪፖርት የማድረግ ኃላፊነት አለበት።
ዝርዝር ተግባርና ኃላፊነት
በምርጫ ቦርድ ግቢ እና አከባቢ፣ ቢሮዎች እና መጋዘኖች ውስጥ ያሉትን የደህንነት ሁኔታ በተገጠሙ ካሜራዎች አማካኝነት የቀጥታ የCCTV ምስሎችን ይከታተላል
ማናቸውንም አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎችን፣ የደህንነት ጥሰቶችን ወይም ያልተፈቀደ ቦታዎች ያሉ እንቅስቃሴዎችን በመለየት እና ለሚመለከተው አካል ሪፖርት ያደርጋል፤
ዕለታዊ የCCTV ክትትል ምዝግብ ማስታወሻዎችን እና የተፈጠሩ ሁኔታዎችን በየእለቱ መረጃ ይይዛል እንዲሁም ሪፖርት ያደርጋል፤
ሁሉም ካሜራዎች እና ተያያ ስርዓቶች በትክክል እየሰሩ መሆናቸውን ያያረጋግጣል፤ ማንኛውንም ቴክኒካዊ ችግሮች ሲፈጠሩ ለIT እና ጠቅላላ አገልግሎት ከፍል ሪፖት ያደርግል፤
በተፈጠሩ የደህንነት ችግሮች ዙርያ አስፈላጊ ምርመራ በሚያስፈልግበት ወቅት በቦርዱ ፍቃድ ሲያገኝ ከደህንነት ካሜራዎች ጋር ባለ ሁኔታ አብሮ ምርመራዎችን ያካሂዳል፤
የምርጫ ቦርድ ንብረት እና ሰራተኞች አጠቃላይ ደህንነት እና ጥበቃ እንዲረጋገጥ የደህንነት/ የጥበቃ ሰራተኞችን ይረዳል፤
የሁሉንም የደህንነት ምስሎች እና ተዛማጅ መረጃዎች ሚስጥራዊነት እና ታማኝነት ይጠብቃል
በሃላፊው የሚሰጠውን ተያያዥ የደህንነት ስራዎችን ይሰራል፡፡
ተፈላጊ ችሎታ
How To Apply
ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ!
Explore more Security, IT, Computer Science and Software Engineering jobs in Ethiopia or browse all available positions on GeezJobs.
Find more jobs in አዲስ አበባ, Addis Ababa.
No related jobs found. Browse all jobs in Ethiopia
Explore other opportunities and find your next job.
View All Jobs in Ethiopia Jobs in አዲስ አበባ, Addis Ababa© 2025 GeezJobs. Made by Geez-Tech.