የግዥ እና ንብረት አስተዳደር አገልግሎት ስራ አስኪያጅ (Manager, Procurement and Property Management Services) - Adiss Ababa, Addis Ababa

TEKHAF Trading PLC

Posted: Jan 17, 2026

Full time

Career Level: Executive(VP, Director)
Salary:
Location: Adiss Ababa, Addis Ababa
Deadline: Jan 28, 2026

Job Opportunity: የግዥ እና ንብረት አስተዳደር አገልግሎት ስራ አስኪያጅ (Manager, Procurement and Property Management Services) position available at TEKHAF Trading PLC in Adiss Ababa, Addis Ababa. Business and Administration, Logistics, Transport and Supply Chain jobs in Ethiopia are in high demand. Apply now through GeezJobs - Ethiopia's leading job portal.

Job Description

·        የስራ መደብ መጠሪያ፦ የግዥ እና ንብረት አስተዳደር አገልግሎት ስራ አስኪያጅ (Manager, Procurement and Property Management Services)

·        የትምህርት ደረጃ፦ የማስተርስ (MA/MSc) ወይም የመጀመሪያ ዲግሪ (BA/BSc) በሰፕላይ ቼይን ማኔጅመንት (Supply Chain Management) ወይም በንብረት አስተዳደር (Property Management)

·        የስራ ልምድ፦ 8 ወይም 10 ዓመት አግባብነት ያለው የማናጅመንት (የስራ አመራር) ልምድ ያለው፤ ቢቻል በንግድ ስራ (Trading Business) ላይ የሰራ ቢሆን ይመረጣል።

1.   የግዢ አፈጻጸም ተግባራትን ማቀድ፣ መምራት፣ መቆጣጠርና፣ ማደራጀት፣

·       የኩባንያውን ስትራቴጂክ እቅድ መሠረት በማድረግ ዓመታዊ እቅድ ያዘጋጃል፣ አፈጻጸሙን ይገመግማል፣

·       በስሩ ያሉ ሰራተኞችን ይመራል፣ ይቆጣጠራል፣

·       የሠራተኞችን የሥራ አፈጻጸም ይገመግማል፣ ውጤታማ የሆኑ ሰራተኞችን ያበረታታል፣ የአቅም ክፍተት ያለባቸውን ሰራተኞች በመለየት ልዩ ድጋፍ እንዲያገኙ ያደርጋል፣

·       የድርጅቱን የአሰራር ችግሮች በመለየትና በማጥናት ምቹ የአሰራር ሂደት እንዲኖር ያደርጋል፣ተፈጻሚነቱን ያረጋግጣል፣

·       ወቅታዊ የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶችን ትክክለኛነት በማረጋገጥ ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፣

·  ዓመታዊ የግዥ ፍላጎት ሰነድ፣ የግዥ እቅድና የሚገዙ እቃዎችን ዝርዝር ስፔስፊኬሽን እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣       

2.   የሀገር ውስጥና የውጭ የግዥ አፈጻጸም ስርዓትን መዘርጋትና ተፈጻሚነቱን ማረጋገጥ፣

·       ግዥዎች በወቅትቱና በስፔስፊኬሽናቸው መሠረት መሆኑን ይከታተላል፣ 

·       ግዥን ለመፈጸም የወጡ አዋጆች ደንቦችና መመሪያዎች በአግባቡ ስራ ላይ መዋላቸውን ያረጋግጣል፣

·       ከየስራ ዘርፉ የሚቀርቡ አስቸኳይ ግዢዎች በደንብና መመሪያ መሰረት  እንዲገዙ ያደርጋል፣

·       ለሚገዙ እቃዎች ተፈላጊው ዓይነት፣ የጥራት ደረጃና መጠን ዝርዝር መግለጫ እንዲወጣ፣  ያደርጋል፣የተገዛውም እቃ ትክክለኛና በወጣው ዝርዝር መግለጫ መሰረት መሆኑን ይከታተላል ፣ያረጋግጣል፣

·       የጨረታ ሰነዶችን በመመርመር በፊርማው አረጋግጦ ለአጽዳቂ ኮሚቴ ይልካል፣

·       የግዢ ውል ሂደት በሚገባ መካሄዱን ይቆጣጠራል፣ ኮንትራታቸውን በአግባቡ የማይወጡትን በመመሪያ መሰረት እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፣

·       ለወሳኝ ዕቃዎች ወጪ ቆጣቢ እና ጥራት ያላቸው አማራጭ ምርቶችን እና አቅራቢዎችን ይለያል።

·        የአገር ውስጥ አቅራቢዎችን የመጠቀም ዕድልን ያሰፋል፤ እንዲሁም ስለ አቅርቦት አፈጻጸማቸው ግብረመልስ ይሰጣል።

·       የግዢና የትራንዚት ስራዎች አስተማማኝ የመንግስት ግዥ አፈጻጸም መመሪያን ተከትሎ መከናወኑን ይከታተላል፣ ያስተባብራል ይመራል፣

·          ልዩ ልዩ የሚያስፈልጉ እቃዎችና አገልግሎቶች በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ በወቅቱ እንዲገዙ በበላይነት ይመራል፣ያስተባብራል፣ ይከታተላል

·     ስለ ግዢ እንቅስቃሴዎ የሚቀርቡትን የተለያየ ዘገባዎችንና ስታትስቲካዊ የሪፖርት መግለጫዎች ያረጋግጣል፣

·   በግዢ አፈጻጸም ላይ ግብረ መልስ መቀበል፣መስጠትና የመፍትሄ እርምጃ መውሰድ፣

3.  የንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ስራዎችን መከታተል

·       የኩባንያውን  የንብረት አስተዳደር፣ የመጋዘን እና የትራንስፖርት ስራዎችን ያቅዳል፣ ያደራጃል፣ ያስተባብራል፣ ይመራል እንዲሁም ይቆጣጠራል።

·       የመጋዘን እና የንብረት አስተዳደር ስራዎች ከኩባንያው ደንቦች፣ መመሪያዎች እና ስልቶች ጋር ሙሉ በሙሉ መጣጣማቸውን ያረጋግጣል።

·       የቡድኑን ስራ በወቅታዊ የዕቃ ዝውውር ሪፖርት ለመደገፍ፣ የክምችት ቁጥጥር (Inventory Control) ስርዓት በሚገባ መደራጀቱን እና መቁጣጠሩን ያረጋግጣል።

·       የንግድ ፍላጎቶችን በየጊዜው በመከታተል፣ የንግድ ስራውን ፍላጎት ለማሟላት የሚያስፈልጉ የቁሳቁስ እና የአገልግሎት ፍጆታዎችን ያመለክታል።

·       በኩባንያው ዋና ስራ አስኪያጅ የሚሰጡ ሌሎች ተመሳሳይ ተግባራትን ያከናውናል።

·       

  የትምህርት ደረጃ፦ የማስተርስ (MA/MSc) ወይም የመጀመሪያ ዲግሪ (BA/BSc) በሰፕላይ ቼይን ማኔጅመንት (Supply Chain Management) ወይም በንብረት አስተዳደር (Property Management)

·        የስራ ልምድ፦ 8 ወይም 10 ዓመት አግባብነት ያለው የማናጅመንት (የስራ አመራር) ልምድ ያለው፤ ቢቻል በንግድ ስራ (Trading Business) ላይ የሰራ ቢሆን ይመረጣል።

How To Apply

interested candidates should submit their resume and a cover letter detailing their relevant experience and qualifications to careers@tekhaftrading.com OR hr@tekhaftrading.com   within 10 working days starting from the announcement day of this vacancy. Please include the job title in the subject line of your e-mail. For any queries, contact us at +251-930294923   

Looking for More Business and Administration, Logistics, Transport and Supply Chain Jobs?

Explore more Business and Administration, Logistics, Transport and Supply Chain jobs in Ethiopia or browse all available positions on GeezJobs.

Find more jobs in Adiss Ababa, Addis Ababa.


© 2025 GeezJobs. Made by Geez-Tech.